Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 106 የቀበሌ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክ/ከተማ ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለሀገር ባለውለታዎችና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች 106 የቀበሌ ቤቶችን አስረክበዋል።

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት÷ከሕዝብ ጋር በተደረገው ውይይት የተሰጡትን ጥቆማዎች መሰረት በማድረግና በማጣራት የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል፡፡

ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የተዘነጉ፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን አቅመ ደካማ ወገኖችን እንባ በማበስና ከነበሩበት አስከፊ ሕይወት በመታደግ ነገን በተስፋ እንዲያዩ የሚያስችል ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።

በተለይም በአራዳ ክ/ከ ቁርጡሚ ወንዝ ዳርቻ ላይ የተነሱ በ3ኛ ወገን ክርክር ምክንያት ሲንገላቱ የቆዩ ነዋሪዎች ዛሬ ችግሩ ተፈትቶ የመኖሪ የቤት በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.