Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት ባለፉት ዓመታት አስደማሚ ውጤቶችን አስመዝግቧል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት አስደማሚ ውጤቶችን አስመዝግቧል አሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ።

‎”የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት በአርባምንጭ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ‎በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ የለውጡ መንግሥት ሰው ተኮርና ለብልፅግና የሚተጋ መንግሥት በመሆኑ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት አስደማሚ ውጤቶችን አስመዝግቧል።

መንግሥት ሰላም፣ መቻቻልና መከባበርን አጥብቆ የሚሻ እንደሆነና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም የሰላምና የመቻቻል ተምሳሌት በመሆኑ እሱን ጠብቆ ማቆየት እንደሚገባ ገልጸው÷ በአንድነትና በሰላም ጉዳይ ላይ የጋሞ አባቶች ሚና የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

የምዕራብ ጉጂ ዞንና የጋሞ ዞን በመነጋገር የነጭ ሳር ፓርክ ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ በኃላፊነት እንደሚሰሩ በማንሳት÷ ‎የፓርኩ ህልውና መጠበቅ ትርፉ የጋራ በመሆኑ ሁለቱ ሕዝቦች አንድ በሚያደርጓቸው መልካም ዕሴቶች በመታገዝ ለውጥ እንደሚመጣ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

‎ከኦሮሚያ ክልል ጉጂና ከጌዲኦ ዞን ዲላ ጋር የሚያገናኘው የመንገድ መሠረተ ልማት ለሰላምና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ወሳኝ በመሆኑ ደረጃውን የጠበቀ የአስፓልት መንገድ እንዲሰራ ጥረት እንደሚደረግ አመላክተዋል።
‌‌‎
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ ገ/መስቀል ጫላ በበኩላቸው÷ ‎እንደ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት በግብርና፣ በኢንዱስትረ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና በከተሞች ላይ ተስፋ ሰጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.