Fana: At a Speed of Life!

የተጀመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የሀገርን ኢኮኖሚ ማቅናት በሚያስችል መልኩ እየተሰሩ ነው – አይሻ መሀመድ (ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተጀመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የሀገርን ኢኮኖሚ ማቅናት በሚያስችል መልኩ እየተሰሩ ነው አሉ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር)።

በወላይታ ሶዶ ከተማ “የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ እንደ ሀገር የተጀመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የሀገርን ኢኮኖሚ ማቅናት በሚያስችል መልኩ እየተሰሩ ይገኛሉ።

በወላይታ ሶዶ አካባቢ በርካታ የተማረ የሰው ኃይል መኖሩን አንስተው÷ የስራ ዕድልን መፍጠር የሚያስችሉ ኢንሼቲቮች እንደ ክልል ሊዋቀሩ ይገባል ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው÷ መንግሥት ከለውጡ ወዲህ የሚታዩ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸው በዚህም ሕዳሴ ግድብን በማጠናቀቅ የሀገራችን ኢኮኖሚ ዋልታ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ስንዴን ከራስ ፍጆታ ባለፈ ለወጪ ንግድ ማቅረብ መቻሉንና የተፈጥሮ ሃብቶችን በዘመነ መንገድ ጥቅም ላይ በማዋል የኢኮኖሚ መሰረት እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በአካባቢው የተጀመሩና የተጠናቀቁ የልማት ስራዎች የብልጽግና ፓርቲ ትሩፋቶች እና የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ውጤቶች ናቸው ያሉት ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ተፈሪ አባተ ናቸው።

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል የተጀመረው የልማት እንቅስቃሴ ውጤት ማምጣቱን እና የአምራች ኢንዱስትሪው ተኪ ምርቶች ላይ እመርታ ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

በመድረኩ የተሳተፉት የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች እንደ ሀገር የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፉ ገልጸው÷ የተለያዩ አገልግሎቶችን በዲጂታላይዜሽን የማዘመን ስራው እንዲስፋፋ ጠይቀዋል።

በመለስ ታደለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast  YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.