የሕዝብን ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው – ሐና አርዓያስላሴ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብን ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው አሉ የፍትህ ሚኒስትሯ ሐና አርዓያስላሴ።
“የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው ዕለት በሰመራ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የሕዝብን ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ በሁሉም አካባቢዎች ያልተነካ እምቅ የመልማት አቅም መኖሩ አንስተዋል።
ወጣቶች ይህንን ፀጋ ጥቅም ላይ በማዋል በሀገራቸው ሰርተው ለመለወጥ በትጋትና በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በሁሉም አካባቢዎች የልማት ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ መንግሥት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በአፋር ክልል የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ ያሉ ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎች ለዚህ ጥሩ ማሳያ መሆናቸውን ገልጸው÷ ከግብርና በተጨማሪ በኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና የዲጂታል ልማት ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ለስኬት እንዲበቁ የጋራ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።
የለውጡ መንግሥት አሳታፊና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት የተረጋገጠባት ጠንካራ ሀገር የመገንባት ዓላማ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን አንስተው÷ በዚህም እመርታዊ ውጤቶች ተመዝግቧል ነው ያሉት።
በመድረኩ የተሳተፉ የሰመራ ሎጊያ ነዋሪዎች ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የአፋር ክልል ሕዝብ የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነቱ በተግባር እውን መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ እየተከናወነ በሚገኘው የግብርና ልማት ስራ ወደ አምራችነት ለመሸጋገር የሚደረገው ጥረት እየተሳካ ነው ብለዋል።
የክልሉ ሕዝብ የፖለቲካ ተሳትፎ፣ የልማት ተጠቃሚነት፣ እኩልነት እና ፍትሃዊነት በተግባር መረጋገጡን በመግለጽ÷ ወጣቱን ማዕከል ያደረጉ የልማትና የስራ ዕድሎች መመቻቸታቸውንም ተናግረዋል።
በተጨማሪም ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ወንጀልን ለመከላከል ወጣቶችን በጥሩ ሥነ ምግባር መቅረጽና በቂ የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!