የተደረጉ የሪፎርም ሥራዎች ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ጉባኤዎችን በስኬት እንድናጠናቅቅ አስችሎናል – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ላይ የተደረጉ የሪፎርም ሥራዎች ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ጉባኤዎችን በስኬት እንድናጠናቅቅ አስችሎናል አሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል።
ጠንካራ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ በሚል መሪ ሃሳብ ለፀጥታና ደኅንነት ተቋማት የምስጋና መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ለተከናወኑ ስኬታማ የህግ ማስከበር ሥራዎችና በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ጉባኤዎች እንዲሁም ሃይማኖታዊ፣ ሕዝባዊና መንግሥታዊ በዓላት በስኬት መካሄዳቸው ተከትሎ ነው መርሐግብሩ የተዘጋጀው።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት÷ ስኬቱ የተመዘገበው በተቋማቱ ላይ በተሰሩ የሪፎርም ሥራዎች እንደሆነ አንስተዋል።
ይህም ለሌሎች ቀጣይ ድሎች በር የከፈተ እንደሆነ ጠቁመው÷ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2027 ኮፕ32 ለማዘጋጀት መመረጧን እንደምሳሌነት ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም በተመሳሳይ ዓመት የአፍሪካ ኢንተርፖል ጉባኤን እንዲሁም በፈረንጆቹ 2028 ደግሞ የዓለም ኢንተርፖል ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጧን አስታውቀዋል።
በቀጣይም ተቋማቱ የሀገርን ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችል ምዕራፍ ላይ በመድረሱ አብሮ መስራቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።
ከባሕር በር ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከውጭ የሚመጡ ትንኮሳዎችን በመረዳት ኢትዮጵያ ዳግም ወደ ባሕር በር የምትመለስበት መንገድን ከመንግሥት እና ከሕዝብ ጋር በመሆን ልናሳካ ይገባልም ነው ያሉት።
በዘመን በየነ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!