Fana: At a Speed of Life!

ለጥበበኞች እውቅና መስጠት የሚያስችለው የጥበባትና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ለጥበበኞች እውቅና መስጠት ያስችላል አሉ፡፡
የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ረቂቅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።
ሚኒስትር ዴኤታው በውይይት መድረኩ እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ አለመኖሩ ሀገር ጥበብን ለምን እንደምትጠቀምበት ግንዛቤ እንዳይኖር አድርጓል።
የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ለጥበብ፣ ለጠቢብ እና ለጥበበኞች ተግባር ዕውቅና ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።
ይህንን ታሳቢ ያደረገ የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ረቂቅ ባለፉት ሶስት ወራት በዘርፉ ባለሙያዎችና የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ሲዘጋጅ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ዘጠኝ ይዘቶችን ያቀፈው ረቂቁ የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ትሩፋቶችን ለማሳደግና በዲጂታል ኢኮኖሚው ግንባታ ላይ በጎ ተፅዕኖ መፍጠር ያስችላል ብለዋል።
የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ በዓለም አቀፍ መድረክ በጥበብ እና ፈጠራ ስራዎች ለመወዳደርና የዲፕሎማሲ ስራን ለመስራት ተጨማሪ እድል የሚፈጥር መሆኑ ተመላክቷል።
በጀማል አህመድ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.