Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ሰባት ዓመታት ጠንካራ ሀገረ መንግሥት እንዲገነባ መሰረት ተጥሏል – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት ባለፉት ሰባት ዓመታት ጠንካራ ሀገረ መንግስት እንዲገነባ መሰረት ጥሏል አሉ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፡፡

“የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች “በሚል መሪ ሃሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በመድረኩ እንዳሉት÷ በመደመር መንግሥት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የጠበቀ እና ዜጎችን ያሳተፈ ጠንካራ የሀገረ መንግሥት ግንባታ እየተከናወነ ነው።

መንግሥት ከህዝብ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ለህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ያለፉትን ሰባት ዓመታት ተሻግሯል በማለት ገልጸው÷ የለውጡ መንግሥት ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ችሏል ብለዋል።

በዚህም በመላው ዓለም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ከፊት የሚቆም ህዝብ እንዲፈጠር አድርጓል ነው ያሉት፡፡

የመደመር መንግሥት የፈጠረው የአንድነት መንፈስ ኢትዮጵያ ከድህነት ተላቃ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን እየተደረገ ያለው ጥረት እየተሳካ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የመደመር መንግሥት ህዝባዊነቱን አጠናክሮ በማስቀጠል እና ዜጎቹን በማዳመጥ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ህዝባዊ ወይይቱ ህዝብና መንግሥት ያላቸውን ቁርኝት በማስቀጠል የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በበኩላቸው÷ መንግሥት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚያደርገው ጥረት ህዝቡ ቀዳሚ ተዋናይ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ህዝባዊ ውይይቶች ጥንካሬን ለማዳበር እና ጉድለቶችን ለማረም ያላቸው ሚና ከፍ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል።

በፍሬው አለማየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.