Fana: At a Speed of Life!

ደረጃቸውን ያልጠበቁ መድኃኒቶች ስርጭትን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት የተጠናከረ አጋርነት ወሳኝ ነው – ዶ/ር መቅደስ ዳባ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ደረጃቸውን ያልጠበቁና ተመሳስለው የተመረቱ መድኃኒቶች ስርጭትን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት የተጠናከረ አጋርነት ወሳኝ ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።

በኢትዮጵያ ደረጃቸውን ያልጠበቁ የመድኃኒት ምርቶችን ስርጭት ለመከላከል የተዘጋጀ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ ተደርጓል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መንግሥት ከሕዝብና ከባለድርሻ አካላት ጋር ባከናወናቸው ተግባራት በሁሉም የጤና አገልግሎት መስኮች አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ከበሽታ መከላከል በተጨማሪ አክሞ ማዳን ላይ ትኩረት ያደረገው አዲሱ የጤና ፖሊሲ ወደ ትግበራ ገብቶ ለውጥ እያመጣ ነው ብለዋል።

የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት እያደገ እና እየተስፋፋ ቢሆንም ጥራት፣ ደህንነት እና ፈዋሽነት የጎደላቸው መድኃኒቶች በገበያ ላይ እንዳይቀርቡ የመከላከል፣ የመለየትና ምላሽ የመስጠት ሥርዓቱን ማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቁጥጥር እና የአቅርቦት ሥርዓቱ እንዲዘምንና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ትኩረት በመስጠት ተጨማሪ አዳዲስ ሥርዓቶችን ለመተግበር በሂደት ላይ ናቸው ብለዋል።

ዛሬ ይፋ የሆነው ከደረጃ በታች ወይም ተመሳስለው የተመረቱ መድኃኒቶችን የመከላከል፣ የመለየት እና ምላሽ የመስጠት ስትራቴጂ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ማጣራትና ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ስትራቴጂው ራሱን የቻለ አሰራር እና አደረጃጀት የሚፈጥር፣ የቁጥጥርና አቅርቦት አቅምን የሚያጠናክር እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን የሚያቀናጅ እንደሆነም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ በበኩላቸው የመድኃኒት ቁጥጥር ዘርፍን ለማሳደግ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸው÷ አዲስ የተዘጋጀው ስትራቴጂ የሕብረተሰብ ጤናን ለመጠበቅ ወሳኝ በመሆኑ የሚመለከታቸው ተቋማት መረባረብ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.