Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሠረተ ልማትን ማስፋፋት የሚያስችለው ስምምነት…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከቻይናው ፓወር ግሪድ ኩባንያ ጋር በኢነርጂና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

በአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) የተመራ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከቻይናው ፓወር ግሪድ ኩባንያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች በኃይል ማስተላለፊያና ማሰራጫ መስመሮች፣ በስማርት ግሪድ ኦፕሬሽን እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዝ ቅድመ ጥገና ሥራ ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

እንዲሁም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሠረተ ልማት ግንባታና በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ ያለውን የኃይል አቅርቦት ለማዘመንና አስተማማኝ ለማድረግ ፈጠራ የታከለበትና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ለመተግበር ቁርጠኛ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል ነው ያሉት፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.