ኦስማን ዴምቤሌ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ሽልማት ሥነ ሥርዓት በተለያዩ ዘርፎች በኳታር ዶሃ ተካሂዷል፡፡
በዚህም የፒኤስጂው የፊት መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡
የባሎንዶር አሸናፊው ዴምቤሌ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፏል፡፡
በአሰልጣኞች ዘርፍ የፒኤስጂ አሰልጣኝ ሊዊስ ኤንሪኬ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል ሲመረጡ፥ ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ተብሎ መመረጡ ይታወቃል፡፡
በሌላ በኩል አይታና ቦንማቲ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች ተብላ መመረጥ ችላለች፡፡
አይታና ቦንማቲ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች ሽልማትን ስታሸንፍ ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ ነው፡፡
በተጨማሪም የፊፋ የዓመቱ ምርጥ 11 ስብስብ ይፋ የተደረገ ሲሆን፥ በዚህም መሰረት ዶናሩማ፣ ኑኖ ሜንዴዝ፣ ቫን ዳይክ፣ ሀኪሚ፣ ፓቾ፣ ፔድሪ፣ ቪቲንሃ፣ ቤሊንግሃም፣ ፓልመር፣ ዴምቤሌ እና ላሚን ያማል በስብስቡ ተካትተዋል፡፡
በፊፋ የዓመቱ ምርጥ 11 ስብስብ ውስጥ ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ራፊንሃ ሳይካተት ቀርቷል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ