ኮንትሮባንድና ሕገ ወጥ የመሬት ወረራን ዜሮ ለማድረስ በቁርጠኝነት ይሰራል – የሐረሪ ክልል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኮንትሮባንድ፣ የመሬት ወረራ እና ሕገ ወጥ ግንባታን ዜሮ ለማድረስ በቁርጠኝነት ይሰራል አለ የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት፡፡
ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተሰጡ አቅጣጫ ግቦች አፈጻጸም ዙሪያ መክሯል፡፡
በዚህም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የቅዳሜ ገበያን በማስፋፋት እንዲሁም የቁጥጥርና ክትትል ሥራዎችን በማጠናከር የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡
የአሰራር ሥርዓትን በማዘመን፣ የዲጂታል አሰራሮችን በማሳደግና ተጠያቂነትን በማስፈን ሌብነትን ለመከላከል በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ተነስቷል፡፡፡
የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎችን ለማሳደግ፣ መንደርተኝነትን ለማስወገድ፣ ጠባቂነትና የጭቃ ቤትን የመቀነስ ስራ በትኩረት እንደሚከናወንም ተጠቁሟል፡፡
በክልሉ የሚታረስ መሬት ፆሙን እንዳያድር በማድረግ በምግብ ራስን ለመቻልና ከተረጂነት ለመላቀቅ የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
ኮንትሮባንድ፣ የመሬት ወረራን እና ሕገ ወጥ ግንባታን ዜሮ ለማድረስ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መጠቀሱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
የገጠር ኮሪደር ሥራን፣ የምርት ማከማቻ ግንባታን፣ የምርት የሽያጭ ማዕከልና አግሮ ፕሮሰሲንግ ግንባታን የማጠናከር እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻዎችን የማስፋት ስራ ላይ ትኩረት እንደሚደረግም ተመላክቷል፡፡
የሌማት ትሩፋትን፣ የበጋ እርሻንና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማሳደግ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማነቃቃት በትኩረት እንደሚሰራ በውይይት መድረኩ ተጠቁሟል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!