ለሀገር ልማት የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና የላቀ ነው – አቶ ጥላሁን ከበደ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሀገር ዕድገት እና ልማት የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና የላቀ ነው አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፡፡
‘ግብር ለሀገር ክብር’ በሚል መሪ ሃሳብ በአርባ ምንጭ ከተማ ለክልሉ ታማኝ ግብር ከፋዮች በዛሬው ዕለት የማበረታቻ እና የእውቅና ሽልማት ተበርክቷል፡፡
አቶ ጥላሁን ከበደ በወቅቱ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳየች ባለው እድገት ላይ የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና የላቀ ነው፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተሰሩ የልማት ስራዎች ላይ የግብር ከፋዮች አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉ ለታማኝ ግብር ከፋዮች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዓለምነሽ ደመቀ በበኩላቸው፤ በክልሉ ታማኝ ግብር ከፋዮችን መሸለም ከጀመርን ወዲህ ‘ግብር የኔ ነው’ የሚል የሕብረተሰብ ክፍል መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡
ግብር በሚሰውሩ እና በታማኝነት በማይከፍሉ ላይ በተደረገ ምርመራ 169 ነጋዴዎች ላይ ርምጃ መወሰዱን አብራርተዋል፡፡
87 ለሚሆኑ ታማኝ ግብር ከፋዮች ደግሞ የማበረታቻ እና የእውቅና ሽልማት በዛሬው ዕለት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በጌትነት ጃርሳ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!