በመዲናዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በሚያጥሩ አካላት ላይ ርምጃ ይወሰዳል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የውስጥ ለውስጥ እና አቋራጭ መንገዶችን በሚያጥሩ ነዋሪዎችና ተቋማት ላይ ርምጃ ይወሰዳል አለ።
ባለስልጣኑ በመንገዶች ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታትና የጋራ መፍትሔ ለማስቀመጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሙህዲን ረሻድ (ኢ/ር) እንዳሉት፤ የውስጥ ለውስጥ እና አቋራጭ መንገዶችን ከማጠር እና በበር ከመዝጋት ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ነገር ግን አሁንም ድረስ የውስጥ ለውጥ መንገዶችን አጥረው ለግል ጥቅም የሚያውሉ አካላት አሉ ብለዋል፡፡
ከአሁን በኋላ ይህንን ተግባር በሚፈጽሙ አካላት ላይ ተገቢው ርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመው፤ የተገነቡ አጥሮችን የማንሳትና ለዚህ ስራ የወጣውን ወጪ በህግ አግባብ የማስመለስ ሥራ ይሰራል ነው ያሉት።
በባለስልጣኑ የምህንድስና የመንገድ ዘርፍ ከፍተኛ አማካሪ አንዳርጌ ክፈተው በበኩላቸው፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶቹ ዝግ መሆን በዋና መንገዶች ላይ ለሚፈጠር የትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት እንደሚሆን ጠቅሰዋል።
የመንገድ ሀብትን ከህገ ወጥ ድርጊት መከላከልና መጠበቅ የሕብረተሰቡ የጋራ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በእየሩሳሌም አበበ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!