Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የቱሪስት መዳረሻዎችን በዓይነትና በጥራት መጨመር ተችሏል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን ባለፉት ዓመታት በተሰራ ስራ የክልሉን የቱሪስት መዳረሻዎች በዓይነትና ጥራት መጨመር ተችሏል አለ።

በኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን ቢሮ አዘጋጅነት በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ የኦሮሚያን እንጎብኝ አካል የሆነ ‘ኮፊ ቱር’ የሳይክል ግልቢያ ተካሂዷል።

የክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ወዳጆ በወቅቱ እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማት ስራ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል።

በዚህም የቱሪስት መዳረሻዎች በዓይነት እና በጥራት መጨመር ተችሏል ነው ያሉት።

የክልሉ ነባር የቱሪስት መዳረሻዎችን ለቱሪስት ምቹ ለማድረግ ከተሰራው ስራ ባሻገር የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው ወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር እና ሎጅን ጨምሮ በርካታ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት ተግባራት መከናወኑን ጠቅሰዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በክልሉ ለቱሪዝም ዘርፉ የሰጠው ትኩረት ውጤታማ እና የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግሥት ለዘርፉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በአብዱረህማን መሀመድ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.