በመዲናዋ ዘመናዊ እና ደረጃቸው የጠበቁ መንገዶች ግንባታ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን ያካተቱ ዘመናዊ እና ደረጃቸው የጠበቁ መንገዶች ግንባታ እየተካሄደ ነው።
መዲናዋን ከዋና ዋና መንገዶች ጋር በሚያስተሳስሩና ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትን በሚያሳልጡ አምስት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።
በምልከታው ከተካተቱት መካከል እያንዳንዳቸው 50 ሜትር ስፋት ያላቸው 14 ነጥብ 73 ኪሎ ሜትር የኮልፌ 18 ማዞሪያ-አሸዋ ሜዳ ኬላ፣ 20 ነጥብ 33 ኪሎ ሜትር የሱሉልታ ኬላ-ሁንዴ ሪዞርት፣ 15 ኪሎ ሜትር የጣፎ አደባባይ-ለገዳዲ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።
ከዚህ በተጨማሪ 4 ነጥብ 73 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር ስፋት ያለው የእንጦጦ ማርያም-ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል እና 9 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 25 ሜትር ስፋት ያለው የእንጦጦ የምርምር ማዕከል-ጫካ መንደር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ምልከታ ተደርጎባቸዋል።
ፕሮጀክቶቹ ከተሽከርካሪ መስመር በተጨማሪ የሳይክል መንገድ፣ የእግረኛ መሄጃ፣ የአገልግሎት መስጫ መስመሮችን፣ የፍሳሽ ማስወገጃዎችን እና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በማካተት ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እየተከናወነ መሆኑ በምልከታው ወቅት ተመላክቷል።
ፕሮጀክቶቹ በመዲናዋ መግቢያና መውጫ በሮች የሚስተዋሉ የትራፊክ መጨናነቅ የሚቀንሱ፣ የግብርና ምርቶችና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ወደ አዲስ አበባና ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በፍጥነት እንዲጓጓዙ በማድረግ ረገድ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው።
በአጠቃላይ አዲስ አበባን ከሸገር ሲቲ ጋር በማገናኘት ረገድ የጎላ ድርሻ ያላቸው መንገዶቹ ጥራታቸውን ጠብቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሆነ ተጠቁሟል።
በቤዛዊት ከበደ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!