Fana: At a Speed of Life!

የማዕድን ዘርፉን በጥናትና ምርምር ለመደገፍ…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕድን ሃብት ለመጪው ትውልድ ዘላቂ የልማት መሰረት እንዲሆን በጥናትና ምርምር ሊደገፍ ይገባል አለ የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ።

በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተሳተፉበት የሥነ ምድር ካርታ ሥራና የማዕድን ፍለጋ ጥናት ውጤቶች ይፋዊ የርክክብ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ 18 አይነት ጥናቶችን በማዘጋጀት የተገኙ የጥናት ውጤቶችን ለክልሉ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ አስረክበዋል፡፡

ሰነዱ በ5 ወረዳዎች የተጠኑ የሥነ ምድር ካርታ ሥራዎች እና ትንተና እንዲሁም በ4 ወረዳዎች የማዕድን ፍለጋና ክምችት ግመታ ጥናትን ያካተተ ነው፡፡

የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ ታምራት ደምሴ እንዳሉት ÷በሀገር በቀል የብዝኃ ኢኮኖሚ አማራጭ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ የሆነው ማዕድን ለኢትዮጵያም ሆነ ለክልሉ ኢኮኖሚ አዲስ የንጋት ተስፋ ሆኗል።

ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚያበረክተውን ድርሻ ለማሳደግና እና ተጠቀሚነትን ለማስፋት በጥናትና ምርምር ሊደገፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በጥናቱ ወርቅን ጨምሮ ጥቁር እብነበረድ፣ እመቲስት፣ ፑሚስ፣ ካልሺዬም ኦክሳይድ፣ ቲታንየም፣ ማንጋኔዝ ኦክሳይድና ሌሎች ማዕድናት መገኘታቸውን አጥኚዎች በጥናታቸው አረጋግጠዋል።

ጥናቱ የክልሉን የሥነ ምድር ጥናት ሽፋን ከ15 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 25 በመቶ ያሳደገ መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.