Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ጉዟችን ከሁሉም በሁሉም ለሁሉም እንዲሆን ይሰራል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና የኢኮኖሚ አቅጣጫ ጉዞ ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም እንዲሆን የማድረግ ስራ ይሰራል አሉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡

አቶ አደም ፋራህ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ በመደመር ፍልስፍና የሚመራው የመደመር መንግሥት በአራት ኢኮኖሚያዊ ሚናዎች ላይ አተኩሮ ይሰራል።

በዚህም የመጀመሪያው ብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ አቅጣጫን መተግበር መሆኑን አንስተው፤ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት፣ ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት የኢትዮጵያን ብልጽግናን የሚያፋጥን ነው ብለዋል።

ሁለተኛው ብዝሃ ተዋናይ አቅጣጫ እንደሆነ ገልጸው፤ በኢኮኖሚ ውስጥ ሚና ያላቸው አካላት የተናጠል እና የጋራ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ሂደት መንግሥት ግንባር ቀደም ሚናውን እንደሚወጣ ጠቅሰው፤ የግል ዘርፉ በማይሳተፍባቸው ዘርፎች መንግሥት ንቁ ኢንቨስተር እንደሚሆን አስረድተዋል።

ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ በሁሉም ዘርፎች ያሉ አቅሞችን የመለየት፣ አቅሞቹን ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻልበትን ስልት መቀየስ እና አቅሞችን ለመጠቀም የሚያስችሉ የኢኮኖሚ አቅጣጫ መከተል ነው ብለዋል።

በዚህም መሰረት በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በአይሲቲ፣ በማዕድን፣ በግብርና ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ውጤት መምጣቱን አብራርተዋል።

ሦስተኛው ብዝኃ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ አቅጣጫ እንደሆነ ያነሱት አቶ አደም፤ ኢኮኖሚው ሁሉም በፍትሃዊነት የሚጠቀምበት እና የሚሳተፍበት እንዲሆን ማድረግ ነው ብለዋል።

በዚህም ለሁሉም እኩል እድል በመፍጠር ተሳትፎውን እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን በማፋጠን ከውጤቱ ሁሉም በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ በመፍጠር የብልጽግና ጉዟችን ከሁሉም በሁሉም ለሁሉም የሆነ እንዲሆን የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በአራተኛ ደረጃ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ትብብርን የማጠናከር አቅጣጫ እንደሆነ ገልጸው፤ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ የሚቻለው ከሌሎች ጋር በመተባበር ነመሆኑን ገልጸዋል።

በኢኮኖሚ መተሳሰር፣ በጋራ ጥቅም ዙሪያ በጋራ መስራት፣ የኢኮኖሚ ውህደት መፍጠር እንዲሁም ፍትሃዊ ስርዓት እንዲኖር እና የሀገር ውስጥ ምርቶች በዓለም ገበያ የተሻለ ዕድል እንዲያገኙ ለማስቻል በትብብር መስራት ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ተናግረዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.