በባሌ ዞን በፈረቃ የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር መፍታት ተችሏል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ለረጅም ጊዜ በፈረቃ የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር መፍታት ተችሏል አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።
በአገልግሎቱ የባሌ ሮቤ ሪጅን ዳይሬክተር በሃሙድ ሁሴን እንዳሉት÷ ከሁለት ዓመት በላይ በባሌ ዞን በሚገኙ ወረዳዎችና ከተሞች በፈረቃ የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የሚፈታ አዲስ ሞባይል ሰብስቴሽን ተከላ ስራ ተጠናቅቋል።
በዞኑ የሚገኙ 8 ወረዳዎችና አካባቢዎቻቸው ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ለረጅም ጊዜ በፈረቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ሲያገኙ መቆየታቸውን አስታውሰው÷ ይህም የተከሰተው በሮቤ ከተማ በተዘረጋው 66 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ የነበረበት የአቅርቦት ውስንነት መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም የዞኑ መቀመጫ ሮቤ ከተማን ጨምሮ ሲናና ወረዳ፣ ጎሮ ወረዳ፣ ዲንሾ ወረዳ፣ አጋርፋ ወረዳ፣ ጋሰራ ወረዳ፣ ጎባ ወረዳ፣ ዳዌ ቃጨል ወረዳና አካባቢዎቻቸው ለረጅም ጊዜ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት በፈረቃ እንደነበር አመላክተዋል።
የዞኑ ነዋሪዎች የኃይል መቆራረጡ እንዲፈታላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ገልጸው÷ አሁን ላይ ለሕብረተሰቡ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ 25 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመር የተገጠመለት ተጨማሪ ሞባይል ሰብስቴሽን ተከላ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ብለዋል።
ይህም አስቀድሞ የነበረውን የ66 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ አቅም በማሳደግና በዞኑ በፈረቃ ሲሰጥ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ከትናንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ መፍታቱን አገልግሎቱ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!