ኢትዮ ቴሌኮም የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማቶችን ለአሸናፊዎች አስረከበ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም 130ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በማስመልከት ያዘጋጀውን ሁለት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማቶች አሸናፊ ለሆኑ ደንበኞቹ አስረክቧል፡፡
ኩባንያው በሽልማት መርሐ ግብሩ ላይ ተጨማሪ ስድስት ዘመናዊ መኪኖችን የሽልማት ዕጣዎችን የማውጣት ሥነ ሥርዓት አከናውኗል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ የሽልማት መርሐ ግብር ከዚህ ቀደም አራት የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንዲሁም 13 ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን (ባጃጅ) ለባለዕድለኛ ደንበኞቹ ማስረከቡን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም 372 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን እና የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብን ጨምሮ በሽልማት መርሐ ግብሩ ከ127 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ አጠቃላይ ዋጋ ያላቸውን ሽልማቶች ሰጥቷል።
ኩባንያው በቀጣይም ደንበኞቹን ተሸላሚ የሚያደርገውን ቴሌ ፕለይ የተሰኘ የሽልማት መርሐ ግብሩን እንደሚያስቀጥልም ተገልጿል።
በኃይለማርያም ተገኝ