Fana: At a Speed of Life!

 ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ተኪ ምርት …

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ተኪ ምርት ለማምረት እየተሠራ እንደሚገኝ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢንቨስትመንት እና አምራች ኢንዱስትሪን የሀገሪቱ የብልጽግና ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

በ2017 በጀት ዓመት በተኪ ምርት 4 ነጥብ 3 ቢሊየን የውጭ ምንዛሪ የተገኘ ሲሆን÷ ዘንድሮ ደግሞ 5 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ነው።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ምርታማነትን ማሳደግና አዳዲስ ባለሃብቶችን መሳብ ተችሏል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራ ቡድን በቅርቡ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ በጎበኘት ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እንዳሉት፤ ወደ ስራ እየገቡ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች በዓይነትም ሆነ በመጠን የተለዩ ስትራቴጂክ ምርቶችን ያመርታሉ።

አምራች ኢዱስትሪዎች ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ ያሉባቸውን ማነቆዎች መለየትና የፖሊሲ መፍትሄ እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል።

ከኃይል አቅርቦት፣ ከግብዓት እጥረት እና ከፋይናንስ ጋር የተገናኙ ችግሮችን ለመፍታትም የሚመለከታቸው ተቋማት በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.