Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ከተረጂነት ወጥተዋል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በምግብ ራሳቸውን በመቻል ከተረጂነት እንዲወጡ ተደርጓል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡

‌‎በአማራ ክልል የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አምስተኛው ምዕራፍ ክልላዊ የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ምርቃት ሥነሥርዓት በዛሬው ዕለት በደብረ ብርሃን ተካሂዷል፡፡

‎የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ እያሱ ኤልያስ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል፡፡

በአማራ ክልል ያለውን ተፈጥሯዊ ሀብት በመጠቀም መስራት ከተቻለ ክልሉን ሙሉ ለሙሉ ከሴፍትኔት ፕሮግራም ማስወጣት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ደረጄ ማንደፍሮ በበኩላቸው፥ በአምስተኛው ምዕራፍ 196 ሺህ 676 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ከሴፍትኔት ፕሮግራም መውጣታቸውን ጠቁመው፥ 630 ሺህ 472 በስራ ላይ የሚገኙ ቤተሰቦች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገራቸውን ተናግረዋል።

‎ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል መርህ ዜጎች ከጠባቂነት እንዲላቀቁ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በኤልያስ ሹምዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.