ብፁዕ ካርዲናል ብርሐነ ኢየሱስ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ሊቀጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሐነ ኢየሱስ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ብርሐነ ኢየሱስ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የልደት በዓል የምስራች የሁሉም መሰረት የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱ እና በኛም መካከል ማደሩ ነው ብለዋል።
የልደት በዓልን ስናከብር ስለሰው ልጆች ክብር የምንሰራበት፣ ሕዝቦች የሚከባበሩበት፣ የሚዋደዱበትና የሚተሳሰቡበት ሊሆን ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች ከቤት ስለራቁት በመፀለይ፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለህሙማን፣ በየጎዳናው ላሉ ወገኖች ያለንን በመስጠትና በማካፈል በዓሉን ማክበር እንደሚገባም የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በቅድስት ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!