Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር እድገት የመንግሥት እና ምሁራን መቀናጀት …

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምሁራን በሀገር ውስጥ እድገት እና ለውጥ ለማምጣት መንግሥት እና ምሁራን ጋር በመቀናጀት ሊሰሩ ይገባል አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ “የምሁራን ሚና ለሀገራዊ ብልጽግና” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ እና የፓናል ውይይት አካሂደዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉት ጽጌ ገብረማርያም (ፕ/ር) እንዳሉት፤ በሀገር እድገት፣ በፖለቲካ፣ በሳይንስ፣ በኢኮኖሚ፣ በሕብረተሰብ እድገት እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ የምሁራን ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

የምሁር ምንነት እና የምሁር የደረጃ እድገት እንዲሁም የሚመራመረው ምርምር ለሕብረተሰቡ ፋይዳ ሊኖረው እንደሚገባው ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አንስተዋል።

የመንግሥት፣ የምሁራን እና የሕብረተሰቡ ቅንጅት እድገት እንደሚያረጋግጥ ገልጸው፤ አብሮ ለመስራት ውይይት መነሻ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ምሁራን የምርምር ውጤታቸው ወደ ተግባር እንዲለወጥ መንግሥትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻዎች ጋር መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

የተቀናጀ ጥረት ፈጠራ ሲታከልበት የሀገር ለውጥ እንደሚመጣ ጠቅሰው፤ የሀሳብ ልዩነት ቢኖርም በመቀራረብ በሀገር ጉዳይ ላይ በአንድነት መቆም እንደሚገባ አመልክተዋል።

ምሁራንን በማሰባሰብም ለጋራ ዓላማ እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ምትኬ ሞላ (ፕ/ር) በበኩላቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ያካሄዱት ውይይት እንደ መሪ ለትምህርት የሰጡትን ትኩረት ያሳያል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው የዓለምን ሂደት ከቴክኖሎጂ ጋር አያይዞ የሚከተል መሆን እንዳለበት በተለይም ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር አብሮ መጓዝ እንዳለበት ግንዛቤ የተወሰደበት መድረክ እንደነበር ጠቅሰዋል።

ምሁራን ራሳችንን ማየት እንዳለብን እና አዳዲስ ሀሳቦችን በመቀበል ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባን የተመላከተበት ውይይት ነበር ብለዋል።

ውይይቱ ዩኒቨርሲቲው ለሀገር እድገት የሚሰጠውን ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያጎላ እንደሆነ ገልጸው፤ ምሁራን መፍትሔ የሚያመነጩ ሊሆን እንደሚገባ የተመላከተበት እንደሆነ አንስተዋል።

በዩኒቨርሲቲው 75ኛ የምስረታ በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) መገኘታቸው ብዙ ነገር የሚያስተምር ነው ያሉት ደግሞ የዓለምፀሃይ መኮንን (ፕ/ር) ናቸው።

መድረኩ በትምህርት መስክ ዓለም የደረሰችበት መድረስና ከዚያም በላቀ ውጤት ለማምጣት መትጋት እንደሚገባ የተመላከተበት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ለዚህም መዘጋጀት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚናቸው ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

የምሁራን እና መንግሥት ቅንጅት ሀገርን መጥቀም እንደሚገባ ጠቅሰው፤ እያደገ የመጣውን የምሁራን እና መንግሥት ትብብርን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.