ላሊበላ የኢትዮጵያውያንን የቆየ የምህንድስና ጥበብ የሚያሳይ ነው – ጎብኚዎች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት ኪነ ሕንጻ የኢትዮጵያውያንን የቆየ የምህንድስና ጥበብ የሚያሳይ ነው አሉ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎች።
የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ለማክበር የተለያዩ ሀገራት ዜጎች በላሊበላ በመገኘት የገና ክብረ በዓልን በመታደም ላይ ይገኛሉ።
ከስፔን እንደመጡ የተናገሩ አንድ ጎብኚ እንደሚሉት፤ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጥንት ጊዜ የተሰራ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ ቴክኖሎጂዎች የተገነቡ የሚመስሉ የጥበብ ውጤቶች ናቸው።
በላሊበላ ሦሥተኛ ቀናቸውን እያሳለፉ የሚገኙት ጎብኚዋ፤ በዛሬው ዕለት በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በውብ ዝማሬ ሲያመሠግኑ መመልከታቸው ልዩ ደስታን እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።
የሀገራቸው ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ይህንን ክብረ በዓል እንዲጎበኙ ያዩትን ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ከሩሲያ የመጡት ሌላኛው ጎብኚ፤ ከአንድ አለት ተፈልፍለው የተሠሩ አብያተ ክርስቲያናትን ለመጀመሪያ ጊዜ በመመልከታቸው መደነቃቸውን ገልጸዋል።
የአካባቢው ማኅበረሠብ ሰላማዊ እና እንግዳ አክባሪነቱ ትኩረታቸውን እንደሳበው አንስተዋል።
የፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ ሥራ የኢትዮጵያውያን የቆየ የምህንድስና ጥበብ የሚያሳይ ነው ያሉት ደግሞ ከእስራኤል የመጡ ጎብኚ ናቸው።
በቀጣይ ቀናት ሌሎች አካባቢዎችን እንደሚጎበኙ በመግለጽ፤ የማኅበረሰቡ እንግዳ ተቀባይነት ማራኪ እንደሆነ መግለጻቸውን የአማራ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!