የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ከተማችንን በጣም ያደመቀ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ከተማችንን በጣም ያደመቀ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ በማሕበራዊ የትስስት ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተካሄደው ‘የአእላፋት ዝማሬ’ አስደናቂ ነው ብለዋል።
የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ከተማችንን በጣም ያደመቀ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ 3ኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር በመስቀል አደባባይ በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ታድመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!