በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱ በጊዜው እንዲካሄድ የባለድርሻዎች ሚና …
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱ በጊዜው እንዲካሄድ በክልሉ የሚገኙ ባለድርሻዎች በትብብር ሊሰሩ ይገባል አለ።
የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በሀገራዊ ምክክር ሂደት የትግራይ ክልል በማካተት ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖረው ለማድረግ የሚከናወኑ ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ለዚህም በቅርቡ የኮሚሽኑ ልዑክ ቡድን ወደ መቐለ ተጉዞ ከሚመለከታቸው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እና ባለድርሻዎች ጋር በመምከር የምክክር ሂደቱን በክልሉ ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት ማድረጉን አስታውሰዋል።
በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከኮሚሽኑ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ ከተመደቡ ሰዎች ጋር አካታችነትና አሳታፊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥነ ዘዴዎችን የማጥናት እና ምክረ ሀሳቦችን የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ምክረ ሀሳቦቹ ለኮሚሽኑ ቀርበው በማጽደቅ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ የምክክር ሂደቱን ውጤታማ ማድረግ በሚችሉ ሥነ ዘዴዎች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባትን እንደሚጠይቅ አንስተዋል።
በምክክሩ አስፈላጊነት ላይ ሕብረተሰቡ ያለውን ፍላጎት የገለጸበት ሁኔታ መኖሩን ጠቅሰው፤ አሁንም የተወሰኑ ተግዳሮቶች መኖራቸውን አመልክተዋል።
በአሁኑ ወቅት ተሳታፊዎችን ለመለየት እና ወደ አጀንዳ ማሰባሰብ ለመግባት በቁልፍ ጉዳዮች መግባባት ላይ ለመድረስ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር መሬት ላይ ለማውረድ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
በጥር ወር መጀመሪያ ቀናት ላይ በክልሉ የተሳታፊዎች ልየታ እና የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱን ለማከናወን ዕቅድ መያዙን ጠቅሰው፤ ዕቅዱን ለመተግበር በክልሉ የሚገኙ ባለድርሻዎች የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ያለውን ጊዜ በመጠቀም ስራውን ለመስራት የጋራ እቅድ በማውጣት በትብብር መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!