Fana: At a Speed of Life!

የእኛ የትግል ስልት ዛሬ ሰርተን ነገን መዋጀት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የትግል ስልት ተለውጧል፤ የእኛ የትግል ስልት ዛሬ ሰርተን ነገን መዋጀት ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራን አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ በቅጡ ተግተን ነገን ለልጆቻችን የሰመረ እና የተሻለ ማድረግ ነው ብለዋል።

የገጠሙን ጠላቶቻችን ትናንትና ላይ ቆመው ዛሬን የሚሻሙ ናቸው በማለት ገልጸው፤ እኛ ዛሬ ሰርተን ነገን ለመዋጀት እንተጋለን ነው ያሉት።

ጠላቶች ትናንት ላይ ቆመው ዛሬን ለመሻማት እንደሚሽቀዳደሙ አስገንዝበው፤ ከጅምሩም ከስልቱም እንደምትመለከቱት በተለያየ ጎዳና የምንጓዝ መንገደኞች ነን ብለዋል።

በመሆኑ አንዱ ለሌላው በተሟላ መንገድ እንቅፋት መሆን እንደማይችል አንስተው፤ ስልታችን የተራራቀ እና የተለየ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በአቢይ ጌታሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.