Fana: At a Speed of Life!

የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ጌዲዮን (ዶ/ር) በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ ከተመራ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት÷ ኢትዮጵያ እና ጃፓን ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው እንዲሁም በሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የግንኙነት መድረኮች ጠንካራ ትብብር እንዳላቸው ገልጸዋል።

ጃፓን ለምታደርጋቸው የልማት ድጋፎች ያመሰገኑት ጌዲዮን (ዶ/ር)÷ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት እየተሻሻለ መምጣቱንና የበለጠ ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከ35 በላይ የጃፓን ኩባንያዎች ለተውጣጡ 48 የቢዝነስ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ ንግድ እና ኢንቨስትመንት አማራጮችን በተመለከተ ገለጻ መስጠታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ እና ጃፓን ግንኙነትን በንግድና ኢንቨስትመንት የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

በነገው ዕለት የኢትዮ-ጃፓን ቢዝነስ ፎረም የሚካሄድ ሲሆን÷ ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.