Fana: At a Speed of Life!

ለጥምቀት በዓል እንግዶቿን መቀበል የጀመረችው ጎንደር…

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የጥምቀት በዓልን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎችና ሀገራት እንግዶች መግባት ጀምሯል አለ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኛው በዓሉን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ የጥምቀት በዓል በተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚከበርና አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

የጥምቀት በዓል በፋሲል ጥምቀተ ባሕር የሚከናወን ሲሆን÷ የዘንድሮ በዓል በጎንደር የመለወጥ ትንሣዔ የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች የአየርና የየብስ ትራንስፖርት መመቻቸቱን  ገልጸው÷ ከ2 ሚሊየን በላይ እንግዶች ይታደማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

በነገው ዕለት የአፄ ቴዎድሮስ ልደት በተለያዩ ኹነቶች እንደሚታሰብ የገለጹት አቶ ቻላቸው÷ የኪን ኢትዮጵያና የባህል ሳምንት የከተማዋ የጥር ወር ድምቀቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች እንግዶችን መቀበል እንደጀመሩና አንድ እንግዳ ለአንድ አባወራ የተሰኘ ፕሮጀክት መዘጋጀቱን አመላክተዋል፡፡

ጥምቀትን ተከትሎ የሚመጡ የሀገር ውስጥና ውጭ ባለሃብቶች በከተማዋ እንዲያለሙ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመው÷ ኢንቨስት ለማድረግ ለሚፈልጉ ባለሀብቶችም 500 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ህይወት በፋሲል አብያተ መንግሥት መርሐ ግብር የዘንድሮው ጥምቀት በዓል አንዱ የትኩረት ማዕከል እንደሚሆን ጠቁመው÷ ይህም የእንግዶችን ቆይታ ለማራዘም ያግዛል ነው ያሉት።

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.