ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር በጁባ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ ለፕሬዚዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከላቸውን ልዩ መልዕክት አድርሰዋል።
ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን÷ ታሪካዊውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
በውይይታቸውም የኢኮኖሚ ትብብርን በተለይም የንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ለመሠረተ ልማት ትስስር ቅድሚያ ትኩረት የመስጠትን አስፈላጊነት አጽንዖት ሰጥተዋል።
የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመንገድ እና የኃይል አቅርቦት ትስስርም ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።