Fana: At a Speed of Life!

የሀገራችንን የፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ ርምጃዎችን ወስደናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገራችንን የፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ ርምጃዎችን ወስደናል አሉ፡፡

ቁልፍ የመንግሥት ፋይናንስና ሌሎች የፋይናንስ ዘርፍ ተቋማትን ያሰባሰበው የኢትዮጵያ የፋይናንስ እመርታ ኮንፈረንስ ‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተካሂዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኮንፈረንሱ በመካሄድ ላይ ያለውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ጉዞ መለስ ብሎ ለመገምገምና የመጪውን ጊዜ የቅድሚያ ምልከታ ለማስቀመጥ የረዳ ጠቃሚ መድረክ ነበር ብለዋል።

የተቋማት ግንባታና ዝግጁነትን ማረጋገጥ የመንግሥት ዐበይት ኃላፊነቶች መሆናቸውን ገልጸው፥ በዚህም መሰረት የሀገራችንን የፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ ርምጃዎችን ወሰድናል ነው ያሉት።

መድረኩ በፊስካል አስተዳደር፣ በሞኒተሪና ፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም፣ በገቢ አስተዳደር፣ በካፒታል ገበያ አስተዳደር፣ በኢንቨስትመንት አስተዳደርና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ሪፎርም ያሳካናቸውን ድሎች ለማጤን ያገዘ ነበር ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የሪፎርሞቹን ጉዞ ፍጥነት አጥብቆ በመያዝ የመራመድንና ሰፊውን የኢኮኖሚ ሽግግር አጀንዳ የማላቅ አስፈላጊነትን ለመገንዘብ የረዳ መድረክ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.