Fana: At a Speed of Life!

ፓርኮቹ ቤተሰብ እና ሕጻናት አስደሳች ጊዜን እንዲያሳልፉ እያደረጉ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንድነት እንዲሁም የወዳጅነት ቁጥር 1 እና 2 ፓርኮች ቤተሰብን እና ሕጻናትን ተቀብሎ አስደሳች ጊዜን እንዲያሳልፉ እያደረጉ ነው አለ አንድነት ፓርክ ኮርፖሬሽን።

ኮርፖሬሽኑ የወዳጅነት ፓርክ ቁጥር 2 ባለው ምቹ የሕጻናት መዝናኛ ሥፍራዎች በዓይነቱ ለየት ያለ እና ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጎብኚዎችን በሚያስተናግደው ፓርኩ ሕጻናት ደስታ የሞላበት ጊዜ እንዲያሳልፉ እና ቆይታቸው ደህንነቱን የጠበቀ እንዲሆን የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች መከናወኑን አውስቷል።

ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ህጻናት ጨምሮ ለልጆች እንክብካቤ የሚያደርጉ እና የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ የሚሰጡ የሕክምና ባለሙያዎችን የማሰማራት፣ ሕጻናትን ጉዳት ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቁሶች ወደ ፓርኩ እንዳይገቡ ማድረግን ጨምሮ ሌሎች ሥራዎች መከናወናቸውን አመላክቷል።

ከተገልጋዮች የአጠቃቀም ጉድለት የመጫወቻዎች እና መገልገያ ቁሳቁሶች ብልሽት እንዳይከሰት የጥንቃቄ ርምጃዎች እንደሚወሰዱ ገልጾ፤ ብልሽት ሲከሰት ተገቢውን ጥገና በማድረግ መልሶ ለአገልግሎት እንደሚያበቃ አስገንዝቧል።

የወዳጅነት አደባባይ ምዕራፍ 2 ጨምሮ ሁሉም መዳረሻዎች ለሁሉም ሰው አስደሳችና ደህንነቱ የተጠበቀ መዳረሻ ሆኖ እንዲቀጥል በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አረጋግጧል።

የአንድነት እንዲሁም የወዳጅነት ቁጥር 1 እና 2 ፓርኮች ጎብኚዎች አስደሳች ጊዜ እንዲያሳልፉ የማድረግ ሥራውን በትጋት እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ ጎብኚዎች ወደ ፓርኮቹ በመምጣት ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ጋብዟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.