Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል የከተማችን የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጥምቀት በዓል የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭ እና የዓለም ሀብት ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ ፍፁም ባማረ መልኩ እንዲከበር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ውይይቱን አስመልክቶ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፤ የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የሚታደሙበት ነው።

በዓሉ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭ እና የዓለም ሀብት ነው ብለዋል።

ከቤተክርስቲያኗ አባቶች እና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ በተደረገው ውይይት አጠቃላይ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን ጠቁመዋል።

አስተዳደሩ እንደ ሌሎች ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ሁሉ የጥምቀት በዓልም በታላቅ ድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.