Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል አለ የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አብዱሰላም መሀመድ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ በተያዘው በጀት አመት በከተማ አስተዳደሩ ገቢን በተገቢው መንገድ ለመሰብሰብ አሰራሮችን በማዘመንና የመፈፀም አቅምን በማሻሻል በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዚህም ከመንግስት ታክስና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከ4 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ39 ነጥብ 86 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ገልጸው፥ በቀጣይ አስተዳደሩን የሚመጥን ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.