የጥምቀትን በዓል በሥራ እያሳለፉ ከሚገኙ ጀግና ሠራተኞች ጋር አብረን ምሳ ተመግበናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ የጥምቀትን በዓል በሥራ እያሳለፉ ከሚገኙ ጀግና ሠራተኞች ጋር አብረን ምሳ ተመግበናል አሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ ከአትላስ – ብራስ፣ ከእንግሊዝ ኤምባሲ – ጎላጎል – ኤድናሞል – ፍሬንድሺፕ፣ ከውኃ ልማት – ሩዋንዳ ድልድይ፣ ከቦሌ መድኃኒዓለም ትምህርት ቤት – አያት ሆስፒታል እና ከአደይ አበባ ስታዲየም – ቦሌ ቀለበት መንገድ ስራ ላይ ከሚገኙ ሰራተኞች ጋር ምሳ መመገባቸውን ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም ከኡራኤል – አትላስ መስመሮች እና በካዛንቺስ የሕፃናት ፓርክ (Children’s Park) በዓሉን በሥራ እያሳለፉ ያሉ በተለያዩ ሳይቶች ላይ ሌት ተቀን በመሥራት ለሀገራችን አዲስ የሥራ ባሕል ያስተዋወቁ ጀግኖችን “እንኳን አደረሳችሁ” ብለን አብረን ምሳ ተመግበናልም ነው ያሉት።
እናንተ ጀግና ወጣቶች፤ የሀገር ፍቅራችሁን በጠንካራ የሥራ ባሕል የገለጻችሁ፣ እጅግ ውብና ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት የሚኖርባትን ከተማ እየገነባችሁ ያላችሁ የሀገራችን ተስፋዎች ናችሁ ሲሉም አመልክተዋል።
ከእናንተ ጋር የጥምቀትን በዓል ማዕድ በመጋራታችን እጅግ ደስተኞች ነን ብለዋል ከንቲባ አዳነች።