Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሀገራት ኢምባሲዎች ለጥምቀት በዓል የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኢምባሲዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ ባስተላለፈው መልዕክት በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የሀሴት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ በበኩሉ÷ በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።

በተጨማሪ የጀርመን፣ የኔዘርላንድስ፣ የእንግሊዝ፣ የጀርመን፣ ስዊዘርላንድ፣ ስዊድን እና ፊንላንድ ሀገራት ኢምባሲዎችን ለጥምቀት በዓል የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

እንዲሁም የእስራኤል፣ አርሜኒያ፣ ካናዳ፣ ኢራን፣ ፓኪስታን እና አውስትራሊያ ኢምባሲዎች በዓሉን አስመልክተው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.