Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ112 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ112 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል አለ።

በኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ጳውሎስ በለጠ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ የኮርፖሬሽኑን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡

በዚህም ባለፉት 6 ወራት ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ112 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።

ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከ2 እጥፍ በላይ እድገት ማሳየቱን ነው የገለጹት።

የኮርፖሬሽኑ የ6 ወራት አፈጻጸም ውጤት ኮርፖሬሽኑ በ5 ዓመት መሪ እቅዱ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጅክ ግቦች ወደ ተግባር እየቀየረ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ የኮርፖሬሽኑን ስትራቴጅክ ግቦች በታቀደው ልክ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሃላፊው አመልክተዋል፡፡

በአድማሱ አራጋው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.