Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከሀገሪቱ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና ከአሜሪካ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በጽሕፈት ቤታችን ከተገኙት የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና የአሜሪካ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተናል ብለዋል።

ቀጣይነት ያለው ትብብር እና መከባበርን አፅንዖት ለሰጠው ደማቅ እና ገንቢ ውይይታችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.