Fana: At a Speed of Life!

ሪፎርሙ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት የአገልግሎት አሰጣጥን ያዘምናል – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት የአገልግሎት አሰጣጥን ያዘምናል አሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን።

የክልሉ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል።

አቶ አሻድሊ በዚሁ ወቅት÷ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል።

የመንግሥት ሰራተኛው የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣትም ዲጂታል ክኅሎቱንና ተወዳዳሪነቱን የሚያሳድግበት ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማስቀጠል የመንግሥት ሠራተኛው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው÷ ሪፎርሙ ነጻና ገለልተኛ ተቋማትን በመፍጠር ተወዳደሪ የሰው ኃይል ለማፍራት ይረዳልም ነው ያሉት።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው÷ ሪፎርሙ ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና ወጪ ቆጣቢ የሥራ ስምሪትን ለመተግበር ያግዛል ብለዋል።

በሪፎርሙ ሰራተኞች በሚሰጣቸው ተልዕኮ መሠረት የሚመዘኑበትና ውጤት ተኮር ሥራ መሥራታቸው የሚረጋገጥበት ሁኔታ እንደሚፈጠር አመላክተዋል።

የሪፎርም ሥራው በቀጣዩ ዓመት ተጠናቅቆ ወደ ትግበራ እንደሚገባም ተጠቅሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.