Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ከአፋሕድ አመራርና አባላት ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩና የሰላምን መንገድ መርጠው ከተመለሱት የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራርና አባላት ጋር እየተወያየ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ነፍጥ ሀገራዊ መግባባትን ሊያሰፍን አይችልም፡፡

ኮሚሽኑ ያከነወናቸውን ዐበይት ተግባራት እንዲሁም በቀጣይ ጊዜያት የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፥ በአማራ ክልል የተከናወነውን የምክክር ሂደት በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ነፍጥ አሸናፊና ተሸናፊን የሚፈጥር እንጂ ሀገራዊ መግባባትን የሚያሰፍን እንዳልሆነ የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፥ ሀገራዊ መግባባት የሚሰፍነው ሁሉም አካላት ስለሀገራቸው ለመመካከር ባላቸው ፅኑ ፍላጎት እንደሆነ አስገዝንበዋል፡፡

ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ቡድኑ ሰላምን በመምረጥ ኮሚሽኑ ሲያቀርባቸው የነበሩ የምክክር ጥሪዎችን በመቀበል ወደ ምክክር መምጣቱ ለሀገራችን ሰላም ትልቅ እምርታ ነው ብለዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ ነፍጥ አንስተው ወደ ጫካ ያስገቧቸውን ጉዳዮች ጨምሮ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች አደራጅተው በዚሁ መድረክ እንደሚያስረክቡ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.