Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ አምራች ፋብሪካዎች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደብረብርሃን ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ አራት አምራች ፋብሪካዎች ተመርቀዋል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ አህመዲን መሐመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የተመረቁት አክሊሉ ክብረት የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ፣ ሁአንግፑ ፕላስቲክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ዱኒያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የፕላስቲክ ጫማ ፋብሪካ እና ማራኪ የዱቄት ፋብሪካ ድርጅቶች ናቸው፡፡

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ በወቅቱ እንዳሉት፤ ባለፉት 6 ወራት በተለያዩ ከተሞች 85 መካከለኛና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ምርት ማስገባት ተችሏል፡፡

በአልሚ ባለሀብቶች የሚነሱ ችግሮችን በመፍታት በኩልም የተሻለ ውጤት መታየቱንም ገልጸዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎቹ 800 ያህል የሥራ እድል የፈጠሩ ሲሆን ተኪ ምርቶችን በማምረትና የውጭ ምንዛሪን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በታለ ማሞ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.