Fana: At a Speed of Life!

የጣሊያን አፍሪካ የጋራ ተጠቃሚነት ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል – ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ሀገራቸው ከአፍሪካ ጋር ያላት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ።

2ኛው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተቋማት ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ በወቅቱ እንዳሉት፤ ጣሊያን እና አፍሪካ የጋራ ግቦችን ለማሳካት በኢነርጂ፣ በትምህርት እና ስልጠና፣ በጤና፣ በዲጂታል መሰረተ ልማት እና ሌሎች መስኮች በትብብር እየሰሩ ነው።

በታዳሽ ሀይል፣ በአረንጓዴ ልማት ሽግግር፣ በምግብ ዋስትና እና ሌሎች መስኮች የሚያደርጉት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት አፍሪካን ከሌላው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ጣሊያን ትሰራለች ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ልማት እና በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ላይ በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ለስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል።

በተለይም ወጣቶች በአህጉራቸው የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ስደትን ለማስቀረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የ”ማቲ ዕቅድ” የአፍሪካን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.