ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከጋና ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጋና ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በሁለተኛው ቀን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ነው የገለጹት።