Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የማምረት አቅም 62 ነጥብ 4 ከመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የማምረት አቅም 62 ነጥብ 4 ከመቶ ደርሷል አሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን አህመድ (ዶ/ር)።

የ’ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት’ ንቅናቄ መድረክ በክልሉ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ባቲ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

አቶ አህመዲን አህመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ከ3 ዓመታት በፊት የአምራች እንዱስትሪ ዘርፍ የማምረት አቅም ከ40 በመቶ የማይበልጥ እንደነበር አስታውሰው÷ አሁን ላይ 64 ነጥብ 2 በመቶ ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ በኋላ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በመፍታትና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሥነ ምህዳር በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪው የማምረት አቅምን ከማሳደግ ባሻገር ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በማስቀረት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪን ማዳን ተችሏል ብለዋል።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ አምራች ባለሃብቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.