Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል የአግሮ ኢንዱስትሪ ስራዎች የግብርና ዕድገታችንን የሚያሳልጡ ናቸው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኦሮሚያ ክልል በአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተጀመሩ ተግባራት የግብርና ዕድገታችንን የሚያሳልጡ ናቸው አሉ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በዛሬው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የነቀምቴ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተናል ብለዋል።

ፓርኩ በኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ250 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ መሆኑን ገልጸው፥ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች ትልቅ የገበያ ዕድል ፈጥሯል ነው ያሉት፡፡

የነቀምቴ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የአርሶ አደሮችን ምርት ተረክቦ በማቀነባበር ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ገልጸዋል፡፡

በግብርና የጀመርነው እመርታ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች ካልተደገፈ ውጤታማ አይሆንም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚህ ረገድ በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ተግባር የግብርና ዕድገትን እንደሚያሣልጥ ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.