Fana: At a Speed of Life!

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ማክበሩን ቀጥሏል።

በምስረታ በዓል አከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ጀኔራል መኮንኖችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዛሬው ዕለትም  የአየር ወለድ፣ ልዩ ኮማንዶ፣ ጸረ ሽብር እና ባሕር ኃይል ክፍሎች በጋራ ከአውሮፕላን የመዝለል፣ የተኩስ እና የገደል ላይ ዝላይ ትርዒት  አቅርበዋል።

በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው ”የውጊያ ማርሽ ቀያሪዎች” በሚል ርዕስ የተፃፈው መጽሐፍ በትናንትናው ዕለት በሀዋሳ ከተማ መመረቁ ይታወሳል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.