Fana: At a Speed of Life!

ለየትኛውም ግዳጅ ዝግጁ የሆነ ጀግና፣ ብቁና ጠንካራ ሠራዊት ተገንብቷል – ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከብሔር እና ፖለቲካ ውግንና ነጻ የሆነ ሠራዊት ተገንብቷል አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፡፡
የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በሐዋሳ በድምቀት ተከብሯል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ከውስጥና ከውጪ የተቃጠባትን የውክልና ጦርነት በተሟላ ቁመና በመመከት አኩሪ ድል አስመዝግባለች ብለዋል፡፡
ከለውጡ በኋላ የመከላከያ ሠራዊት በሁለንተናዊ መንገድ የመፈጸም አቅሙ ማደጉን አውስተው ÷ ባለፉት ዓመታት ለውጡን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ሃይሎችን ከማጽዳት ጎን ለጎን መከላከያ ሠራዊትን እንደ ተቋም የመለወጥ ስራ ተከናውኗል ነው ያሉት፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ያልተደራጀ ሰራዊት በመያዝ የሰሜኑን ጦርነት በሚያስደንቅ ሁኔታ በድል መወጣቱን አስታውሰዋል፡፡
ሠራዊቱ ባለፉት ጊዜያት ውጊያዎችን እያረገ የተገነባ መሆኑን በማንሳት ÷ በንድፈ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በጦርነት ጭምር መሰልጠኑን ጠቁመዋል፡፡
የልዩ ዘመቻዎች እዝ ከብሔር እና የፖለቲካ ውግንና ነጻ የሆነ እዝ መሆኑን ጠቅሰው÷ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የሪፐብሊካን ጋርድን ጭምር አምጦ የወለደ የጦር ሃይል ነው ብለዋል፡፡
የልዩ ዘመቻዎች እዝና የሪፐብሊካን ጋርድን ነጣጥሎ ማየት እንደማይቻልም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
እዙ በዘመናት መካካል በርካታ ገድሎችን መፈጸሙንና የሰሜን እዝን ጥቃት ተከትሎም በነበረው ጦርነት ክፍለ ጦሩ አስደማሚ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
በአቤል ነዋይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.