Fana: At a Speed of Life!

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዛሬ ማለዳ ለእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን እና ለሀገር ሉአላዊነት ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች ታሪክን አስጎብኝተናቸዋል ብለዋል።

ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለነበራቸው ጊዜም አመስግነዋል።

በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ እመኛለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.