ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በባኩ የክብር አደባባይና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባኩ የክብር አደባባይና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት አከናውነዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካቸው በአዘርባጃን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ በትናንትናው ዕለት ባኩ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው በባኩ የክብር አደባባይና የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት አከናውነዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባወጣው መረጃ እነዚህ ሀውልቶች የህዝቡን የማይበገር አንድነት የሚወክሉ መሆናቸውን ጠቅሶ፥ ለአዘርባጃን አንድነት መስዋዕትነት ለከፈሉ ሁሉ ያለንን ጥልቅ ክብር መግለጽ እንወዳለን ብሏል።