Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ስም ላስገነባው ት/ቤት የትምህርት ቁሳቁስ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በአምቦ ከተማ አስተዳደር በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ስም ላስገነባው ት/ቤት የትምህርት ቁሳቁስ ስጦታ አበርክቷል፡፡

የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን 20ኛ አመት የዕረፍት መታሰቢያ መርሐ ግብር በትናንትናው ዕለት በአምቦ ከተማ ተካሂዷል።

ጽ/ቤቱ በዚሁ ወቅት ለሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን የኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ መፅሀፍት፣ የሚኒ ሚዲያ ቁሳቁሶች፣ የንፅህና መጠበቂያና ሌሎች ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ ግብአቶች በስጦታ አበርክቷል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መፅሀፍት ሽያጭ በተገኘ ገቢ በ2015 ዓ.ም በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነባው ት/ቤቱ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

በሲሳይ ሀይሌ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.